በዚህ ሳምንት (ከኅዳር 21 እስከ ኅዳር 27) ከተከናወኑ አገራዊና ዓለም አቀፋዊ ታሪካዊ ክስተቶች መካከል፡-
ኅዳር 21 ቀን 1853 ዓ.ም – ከ1897 ዓ.ም ጀምሮ በበርሊን ዩኒቨርስቲ አማርኛና ግዕዝን ያስተማሩት፤ ‹‹በጀርመን ሀገር የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ መምህር›› በመባል የሚታወቁት፣ በርካታ መጽሐፍትን የደረሱትንና አገራቸው ኢትዮጵያ ከኋላቀርነት ተላቅቃ እንደ እንድትሰለጥን ምሁራዊ ምክረ ሀሳብ በማቅረብ ብዙ ጥረት ያደረጉት ሊቁ አለቃ ታዬ ገብረማርያም ተወለዱ፡፡
አለቃ ታዬ በመምህርነት፣ በአስተርጓሚነትና በወንጌል ሰባኪነት አገልግለዋል፡፡ ‹‹መጽሐፈ ሰዋሰው›› የተባለውን መጽሐፍ የፃፉት እርሳቸው ናቸው፡፡ የጀርመን መንግስት የግዕዝ ቋንቋ የሚያስተምር አንድ ሊቅ እንዲሰጠው ለዳግማዊ አጼ ምኒልክ ጥያቄ ባቀረበበት አለቃ ታዬ ተመርጠው ወደ ጀርመን ሄዱ፡፡ በጀርመንምለሶስት ዓመታት ያህል የግዕዝ ቋንቋ አስተምረው ኒሻን ተሸልመው ወደ ኢትዮጵያ ተመለሱ፡፡ አጼ ምኒልክም ኒሻን ሸለሟቸው፡፡
አለቃ ታዬ በኢጣሊያና በፈረንሳይም ተዘዋውረው ብዙ ከተሞችን ጎብኝተዋል፤የሕዝቡን ባሕል ተመልክተዋል፡፡ የወቅቱን የአውሮፓን ስልጣኔና አጠቃላይ ሁኔታም ታዝበዋል፡፡ በጀርመን ቆይታቸው በበርሊን ዩኒቨርስቲ አማርኛንና ግዕዝን ከማስተማር በተጨማሪ ከኢትዮጵያ የሄዱ በግእዝ የተጻፉ መጽሐፍትን በመሰብሰብ መርምረዋል፡፡
አለቃ ታዬ የበርካታ መጽሐፍት ባለቤት ቢሆኑም አብዛኛዎቹ ስራዎቻቸው ወደ ሕዝብ እጅ አልደረሱም፡፡ ከስራዎቻቸው መካከል ‹‹መጽሐፈ ሰዋሰው››፣ እስከ አሁን ድረስ በስዊዲንኛ ቋንቋ ብቻ የሚገኘውና በወጣትነት ዘመናቸው እንደጻፉት የሚገመተው ‹‹ነገረ መለኮታዊ ክርክር በራስ መንገሻ ችሎት›› (en Teologisk strid infor Ras Mengescha" (A Theological Debate Before Ras Mengesha)፣ በዕድሜ ዘመናቸው ማብቂያ ላይ ሳይደርሱት እንዳልቀረ የሚነገረው ‹‹የአማርኛ መዝገበ ቃላት (የጽንሰ ሐሳብ መዝገብ)›› እና ሌሎችም ተጠቃሽ ናቸው፡፡
ምሁሩ አለቃ ታዬ የሕይወት ዘመናቸውን ለአገራቸው ብዙ በማበርከት ከእንግልት ጋር ካሳለፉ በኋላ ነሐሴ 15 ቀን 1916 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡
ኅዳር 21 ቀን 1867 ዓ.ም – የጦር መሪና ጋዜጠኛ የነበሩት፣ በስነ-ጽሑፍ የኖቤል ሽልማትን ያሸነፉትና እንግሊዝን ለ10 ዓመታት ያህል በጠቅላይ ሚኒስትርነት ያገለገሉት ሰር ዊኒስተን ሊዮናርድ ስፔንሰር ቸርቺል ተወለዱ፡፡ ዊኒስተን ቸርቺል እ.አ.አ ከ1940 እስከ 1945 እና ከ1951 እስከ 1955 ድረስ እንግሊዝን በበጠቅላይ ሚኒስትርነት መርተዋል፡፡
በአውሮፓ ሊብራል ዴሞክራሲ ጠበቃነታቸውና በፀረ-ፋሺስት አቋማቸው በመላው ዓለም የሚታወቁት ዊኒስተን ቸርቺል፤ ኢትዮጵያ ውስጥ በስማቸው ጎዳና (‹‹ቸርቺል ጎዳና››) ተሰይሞላቸዋል፡፡ ዊኒስተን ቸርቺል ያረፉት በ1957 ዓ.ም ነው፡፡
ኅዳር 22 ቀን 1903 ዓ.ም – በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ዘመናዊ መድኃኒት ቤት (ፋርማሲ) ተከፈተ፡፡ መድኃኒት ቤቱን የከፈቱት ዶክተር ፖል ሜራብ የተባሉ የጆርጂያ ተወላጅ ሃኪምና ተመራማሪ ነበሩ፡፡ የመድኃኒት ቤቱ ስም ደግሞ ‹‹የጊዮርጊስ/የጆርጂያ ፋርማሲ›› ይባል ነበር፡፡
የፈረንሳይ ዜግነት የነበራቸው ዶክተር ሜራብ፣ በህክምና ሙያቸው በቁስጥንጥንያ ሲያገለግሉ በነበረበት ወቅት ከኢትዮጵያውያን የልዑካን ቡድን አባላት ጋር ተዋውቀው ስለነበር ወደ ኢትዮጵያ መጥተው የንጉሰ ነገሥት ዳግማዊ አፄ ምኒልክ የግል ሐኪም ሆነው አገልግለዋል፡፡
ኅዳር 22 ቀን 1987 ዓ.ም – ደራሲ፣ የሥነ-ጽሑፍ መምሕር፣ ገጣሚ እና የተውኔት ጠቢብ የነበረው ዳኛቸው ወርቁ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ፡፡ ዳኛቸው አደፍርስ፣ እምቧ በሉ ሰዎች፣ ሰቀቀንሽ እሳት፣ ሰው አለ ብዬ፣ ትበልጭ፣ ያላቻ ጋብቻ፥ትርፉ ሐዘን ብቻ፣ ማሚቴ፣ The Thirteenth Sun እና የጽሑፍ ጥበብ መመሪያ በተባሉ የልብወልድ፣ የተውኔትና የምርምር ስራዎቹ ይታወቃል፡፡
ኅዳር 24 ቀን 1966 ዓ.ም – ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ስራ (አገልግሎት መስጠት) ጀመረ፡፡ የሆስፒታሉ ግንባታ የተጀመረው በ1950ዎቹ መጨረሻ ላይ ሲሆን ግንባታው 21 ሚሊዮን 605 ሺህ 399 ብር ወጥቶበታል፡፡ የሆስፒታሉ የመጀመሪያ ስም ‹‹የልዑል መኮንን መታሰቢያ ሆስፒታል›› ነበር፡፡ ወታደራዊወ ቡድን (ደርግ) ስልጣን ከያዘ በኋላ የሆስፒታሉ ቀድሞ ስም ተቀይሮ ከ1968 ዓ.ም ጀምሮ ‹‹ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል›› ተብሎ መጠራት ጀመረ፡፡
‹‹ጥቁር አንበሳ›› በፋሺስት ኢጣሊያ ወረራ ወቅት ከፍተኛ መስዋትነት የከፈሉትና በ1928 ዓ.ም የተመሰረተው የሆለታ ገነት የጦር ትምህርት ቤት የመጀመሪያዎቹ ምሩቆች የነበሩ ወጣት አርበኞች የትግል ስም ነው፡፡ ሆስፒታሉ በዚህ ስም እንዲጠራ የተደረገው የእነዚያን ወጣት አርበኞች ጀግንነትና የአገር ፍቅር ስሜት እንዲታወስና ለትውልዶች እንዲተላለፍ ታስቦ ነው፡፡
ኅዳር 25 ቀን 1560 ዓ.ም – የአጤ ልብነ ድንግል ባለቤት የነበሩትና በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ከፍ ያለ ቦታ ከያዙ ተፅዕኖ ፈጣሪ እንስቶች መካከል ተጠቃሽ የሆኑት እቴጌ ሰብለወንጌል አረፉ፡፡
ኅዳር 26 ቀን 1927 ዓ.ም – ፋሺስት ኢጣሊያ ኢትዮጵያን ለመውረር እንደሰበብ የተጠቀመችበት ታሪካዊው የወልወል ግጭት ተከሰተ፡፡ ኅዳር 26 ቀን 1927 ዓ.ም በኢጣሊያ ሱማሌላንድ የነበሩ የኢጣሊያ ወታደሮች በኢትዮጵያ እና በእንግሊዝ ሱማሌላንድ መካከል ያለውን ወሰን ለመከለል የተላኩትን ሰዎች ይጠብቁ በነበሩት የኢትዮጵያ ወታደሮች ላይ ጥቃት ከፈቱባቸው፡፡ ውጊያ ተደረገና በሁለቱም ወገኖች በኩል የሞትና የአካል ጉዳት ደረሰ፡፡ ኢትዮጵያም ስሞታዋን ለኢጣሊያ መንግሥት ስታቀርብ፤ የኢጣሊያ መንግሥት ይባስ ብሎ የተበደለ መሆኑን በመግለፅ ካሳ እንዲከፈለው ጥያቄ አቀረበ፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥትም የኢጣሊያን ሃሳብ ሳይቀበል ቀረ፡፡ ከዚህ በኋላ ፋሺስት ኢጣሊያ ለ40 ዓመታት ያህል ስትዘጋጅበት የቆየችውን እቅድ እውን ለማድረግ በሁሉም አቅጣጫዎች ኢትዮጵያን ወረረች፡፡
ኅዳር 26 ቀን 1996 ዓ.ም – ደራሲ፣ መምህር፣ ፖለቲከኛ፣ አርበኛና ባለቅኔ የክብር ዶክተር ሀዲስ ዓለማየሁ አረፉ፡፡ ‹‹ሀበሻና የኋላ ጋብቻ››፣ ‹‹ተረት ተረት የመሰረት››፣ ‹‹ፍቅር እስከ መቃብር››፣ ‹‹ወንጀለኛው ዳኛ››፣ ‹‹የልም ዣት››፣ ‹‹ትዝታ›› በሚሉትና በሌሎችም ስራዎቻቸው ተወዳጅነትንና ታዋቂነትን ያተረፉት የክብር ዶክተር ሀዲስ ዓለማየሁ፣ በኢትዮጵያ ስነ-ጽሑፍ ላይ ያሳረፉት አሻራና ያበረከቱት አስተዋፅኦ እጅግ ላቅ ያለ ነው፡፡በዚህ ሳምንት (ከታኅሳስ 5 እስከ ታኅሳስ 11) ከተከናወኑ አገራዊ ታሪካዊ ክስተቶች መካከል በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሰው ቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሴን ከስልጣን ለማስወገድ የተጠነሰሰው የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ነው፡፡ ይህ ታሪካዊ ክስተት በተለምዶ ‹‹የታኅሳስ ግርግር›› በመባል ይታወቃል፡፡ ከመፈንቅለ መንግሥት ጠንሳሾቹ መካከል ጎልተው የሚጠቀሱት ወንድማማቾቹ ብርጋዴር ጀኔራል መንግሥቱ ነዋይ (የክብር ዘበኛ ጦር አዛዥ) እና ግርማሜ ነዋይ ናቸው፡፡ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራው የተጀመረው ታኅሳስ 4 ቀን 1953 ዓ.ም ሲሆን በወቅት ንጉሰ ነገሥቱ ለጉብኝት ወደ ብራዚል ሄደው ነበር፡፡
ታኅሳስ 5 ቀን 1953 ዓ.ም – የመፈንቅለ መንግሥት ጠንሳሾቹ ዓላማቸውን ይፋ አደረጉ። ለውጥ ፈላጊ ናቸው የሚባሉትን ልዑል ራስ እምሩ ኃይለ ሥላሴን በጠቅላይ ሚኒስትርነት መሾማቸውንና አልጋ ወራሹን አስፋ ወሰንን (‹‹አስገድደው››) በማስማማትም መንግሥት በቆረጠላቸው ደመወዝ እየተዳደሩ ለሕገ መንግሥት የሚገዙ ንጉሥ ሆነው እንደሚያገለግሉ እራሳቸው ለሕዝቡ በሬዲዮ እንዲያስተላልፉ አደረጉ።
ታኅሳስ 6 ቀን 1953 ዓ.ም – የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራውን የሚቃረነው የነሌተናል ጀኔራል መርድ መንገሻ ኃይል ዝግጅቱን ጨርሶ በዚያው ዕለት ከቀትር በኋላ በዓየር እና በታንክ ጭምር የተፋፋመ ውጊያ ሲጀምር ብርጋዴር መንግሥቱ ነዋይ መምሪያ ክፍላቸውን ወደ ገነተ ልዑል ቤተ መንግሥት አዛወሩ።
ታኅሳስ 7 ቀን 1953 ዓ.ም – የመፈንቅለ መንግሥት ጠንሳሾቹ ኃይል እየተዳከመ በአንጻሩ ደግሞ ተቃዋሚዎቻቸው እያደር እየጠነከሩ መሄዳቸውን የተገነዘቡት እነብርጋዴር ጀኔራል መንግሥቱ፤ በቁጥጥራቸው ስር የነበሩትን 20 መሳፍንት፣ መኳንንት፣ ሚኒስትሮችንና የጦር መኮንኖችን ወደ አረንጓዴ ሳሎን አዛውረው አልጋወራሹንና አዲሱን ጠቅላይ ሚኒስትር ለብቻቸው እንዲጠበቁ አደረጉ። ብርጋዴር ጀኔራል ጽጌ ዲቡ ወዲያው ከተቃራኒ ወገን በተተኮሰ ጥይት ሲገደሉ፣ እነ ጀኔራል መንግሥቱ የያዟቸውን እስረኞት ገድለው ለማምለጥ ወሰኑ፡፡ በዚህም መሰረት ሜጄር ጀኔራል ሙሉጌታ ቡሊ፤ ራስ ስዩም መንገሻ፤ ራስ አበበ አረጋይ፤ አቶ መኮንን ሀብተወልድ፤ አባ ሐና ጅማ፤ በጠቅላላው 15 ሰዎች ተገደሉ። የክብር ዘበኛ መኮንን የነበሩት ሻምበል ደረጀ ኃይለ ማርያም የመፈንቅለ መንግሥት ሞካሪዎችን በመቃወም የቤተ መንግሥቱን አጥር በታንክ ደምስሰው ሲገቡ ከጠንሳሾቹ ወገን በተተኮሰ ጥይት ተገደሉ።
ታኅሳስ 8 ቀን 1953 ዓ.ም – የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራው ተደምስሶ (ከሽፎ) ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሴ ለጉብኝ ከሄዱበት ከብራዚል ተመልሰው በአስመራ በኩል አዲስ አበባ ገቡ።
ታኅሳስ 8 ቀን 1896 ዓ.ም – ኦርቪል ራይት እና ዊልበት ራይት የተባሉት አሜሪካውያን ወንድማማቾች የመጀመሪውን የተሳካ የአውሮፕላን ፈጠራ ስራ ሰርተው አጠናቀቁ፡፡በዚህ ሳምንት (ከታኅሳስ 12 እስከ ታኅሳስ 18) ከተከናወኑ አገራዊ ታሪካዊ ክስተቶች መካከል:-
ታኅሳስ 12 ቀን 1929 ዓ.ም – ፋሺስት ኢጣሊያ ኢትዮጵያን በወረረችበት ወቅት ለሀገራቸው ክብርና ነፃነት በአርበኝነት ሲታገሉ የነበሩት ወንድማማቾቹ ደጃዝማች አበራ ካሣ እና ደጃዝማች አስፋወሰን ካሣ ተገደሉ፡፡
ደጃዝማች አበራ ካሣ እና ደጃዝማች አስፋወሰን ካሣ በቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግሥት ወቅት ከፍተኛ ተሰሚነት የነበራቸው የልዑል ራስ ካሣ ኃይሉ ልጆች ናቸው፡፡ ጀግኖቹ ወንድማማቾች የቀዳማዊ አጤ ኃይለሥላሴ ጦር ማይጨው ላይ ‹‹ሽንፈት›› ካጋጠመው በኋላ ኢትዮጵያውያንን በየአካባቢው በማሰለፍ የነፃነት ትግል ከጀመሩት አርበኞች መካከል ዋነኞቹ ነበሩ፡፡
በ1929 ዓ.ም በተለያዩ አካባቢዎች ከፋሺስት ወታደሮች ጋር ውጊያ ላይ የነበሩት አርበኞች ከሁሉም አቅጣጫዎች ወደ አዲስ አበባ በመገስገስ በፋሺስት ኢጣሊያ ላይ ጥቃት ለመክፈት እቅድ አወጡ፡፡ ነገር ግን በወቅቱ በቂና ዘመናዊ የሆነ የቁሳቁስ አቅርቦት ያልነበራቸው ኢትዮጵያውያን አርበኞች እንዳሰቡት ሳይሆንላቸው ቀረ፤ የማጥቃት ዘመቻው ቅንጅት የጎደለው ስለነበር ጥቃት የከፈቱት አርበኞችም መጨረሻቸው ሞትና ሽሽት ሆነ፡፡ በወቅቱ የፋሺስትን ጦር ሲወጉ ከነበሩት የአርበኞች መሪዎች መካከል ወንድማማቾቹ ደጃዝማች አበራ ካሣ እና ደጃዝማች አስፋወሰን ካሣም እጅ እንዲሰጡ ተጠየቁ፡፡
ወቅት ለፋሺስት አስተዳደር እውቅና ሰጥተው የነበሩት ራስ ኃይሉ ተክለኃይማኖት እና ራስ ስዩም መንገሻ ወንድማማቾቹ እጃቸውን እንዲሰጡና ምንም ዓይነት ቅጣት እንደማይፈፀምባቸው ለጀግኖቹ ወንድማማቾች ነገሯቸው (ቃል ገቡላቸው)፡፡ ደጃዝማች አበራ ካሣ እና ደጃዝማች አስፋወሰን ካሣም እነ ራስ ኃይሉ ተክለኃይማኖትን አምነው እጃቸውን ሰጡ፡፡ ይሁን እንጂ ቀድሞም ቢሆን ታማኝነታቸውን ለፋሺስት አስተዳደር ያሳዩት እነ ራስ ኃይሉ ተክለኃይማኖት፣ ጀግኖቹን ወንድማማቾች ለፋሺስት ኢጣሊያ ባለስልጣናት አሳልፈው ሰጥተው በጥይት ተደብድበው እንዲገደሉ አደረጉ፡፡
የደጃዝማች አበራ ካሣ ባለቤት ታላቋ አርበኛ ክብርት ወይዘሮ ከበደች ሥዩም (የራሥ ሥዩም መንገሻ ልጅ) ናቸው፡፡ ታላቋ አርበኛ የባለቤታቸውንና የባለቤታቸውን ወንድም መገደል በሰሙ ጊዜ ልጃቸውን ልጅ ዓምደጽዮን አበራን ይዘው የአርበኝነት ተጋድሏቸውን ጀመሩ፡፡ አርበኛ ከበደች ባለቤታቸውንና የባለቤታቸውን ወንድም እንዲሁም ሌሎች ወገኖቻቸውን የገደለባቸውን የፋሺስት ኢጣሊያ ኃይል ከሌሎች ኢትዮጵያውያን አርበኞች ጋር በጋራ በመተባበር ድል አድርገው የኢትዮጵያን ነፃነት አስከብረዋል፡፡
ታኅሳስ 14 ቀን 1928 ዓ.ም – ወራሪው የፋሺስት ኢጣልያ ጦር በኢትዮጵያ ሠራዊት ላይ የመርዝ ጭስ (ጋዝ) መርጨት ጀመረ:: የመርዝ ጋዙ የተረጨውም በራስ እምሩ ኃይለሥላሴ በሚመራው ጦር ላይ ነበር፡፡
ወራሪው የፋሺስት ኢጣልያ ጦር በኢትዮጵያውያን ላይ የተጠቀመው በዓለም አቀፍ ሕግጋት የተከለከለውን የመርዝ ጭስ (ጋዝ)፣ የኢትዮጵያንና የኢትዮጵያውያንን ማኅበረ-ኢኮኖሚያዊ፣ ስነ-ልቦናዊና ፖለቲካዊ ሁኔታ የለወጠ ነበር፡፡
ታኅሳስ 17 ቀን 1980 ዓ.ም – ኢትዮጵያ የምሥራቅና መካከለኛው አፍሪካ የእግር ኳስ ሻምፒዮና ዋንጫ (ሴካፋ/CECAFA)ን ለመጀመሪያ ጊዜ አሸነፈች፡፡
ኢትዮጵያ ባስተናገደችውና ስምንት አገራት (ኢትዮጵያ፣ ዚምባብዌ፣ ዛንዚባር፣ ኬንያ፣ ታንዛኒያ፣ ኡጋንዳ፣ ዛምቢያ እና ማላዊ) በተካፈሉበት 15ኛው የምሥራቅና መካከለኛው አፍሪካ የእግር ኳስ ሻምፒዮና ዋንጫ (ሴካፋ/CECAFA) ለፍፃሜ የቀረቡት አስተናጋጇ ኢትዮጵያ እና ዚምባብዌ ነበሩ፡፡
ታኅሣሥ 17 ቀን 1980 ዓ.ም የፍፃሜው ጨዋታ የተካሄደበት ቀን ነበር፡፡ መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜው 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቆ በተሰጡት የመለያ ምቶች ኢትዮጵያ አሸንፋ የዋንጫ ባለቤት ሆነች፡፡ በወቅቱ ጨዋታውን ሲያስተላልፍ ከነበረው ከአንጋፋው ጋዜጠኛ ደምሴ ዳምጤ አንደበት የተሰማው ሳቅና እንባ የተቀላቀለበት የደስታ ጩኸት ዛሬም ድረስ ከበርካታ ኢትዮጵያውያን አዕምሮ የሚጠፋ አይደለም፡፡
በዕለቱ ዋንጫውን ለብሔራዊ ቡድኑ አምበል ገብረ መድኅን ኃይሌ የሰጡት የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ (ኢ.ሕ.ዲ.ሪ) ፕሬዝደንት፣ሌተናል ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም 100 ሺሕ ተመልካች የሚይዝ ስታዲየም እንደሚሰራ ቃል ገብተው ነበር፡፡በዚህ ሳምንት (ከታኅሳስ 19 እስከ ታኅሳስ 25) ከተከናወኑ አገራዊ ታሪካዊ ክስተቶች መካከል:-
ታኅሳስ 19 ቀን 1962 ዓ.ም – በኢትዮጵያ የተማሪዎች እንቅስቃሴ (ትግል) ውስጥ ቀዳሚ ስፍራ የነበረው ጥላሁን ግዛው ተገደለ፡፡ ጥላሁን ግዛው የተወለደው በ1933 ዓ.ም ነው፡፡ ቤተሰቦቹ በዘመኑ ‹‹ባላባት›› ተብሎ ከሚጠቀሰው የኅብረተሰብ ክፍል ውስጥ የሚመደቡ ነበሩ፡፡ የመጀመሪያና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በወልድያ እና በአዲስ አበባ ካጠናቀቀ በኋላ ኮተቤ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ገብቶ ትምህርቱን በከፍተኛ ውጤት በማጠናቀቅ በ1959 ዓ.ም. የቀድሞው ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ (ቀ.ኃ.ሥ) ዩኒቨርሲቲ (የአሁኑ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ) የፖለቲካ ሳይንስ ትምህርት ክፍል መግባት ቻለ፡፡
በዩኒቨርሲቲውም በየደረጃው ባሉ ክበባትና አደረጃጀቶች በመሳተፍ በኢትዮጵያ የተማሪዎች እንቅስቃሴ (ትግል) ውስጥ ቀዳሚ ስፍራ መያዝ ቻለ፡፡ በኅዳር 1962 ዓ.ም. በወቅቱ ዝነኛ የነበረው የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ማህበር ፕሬዝደንት ሆኖ ተመረጠ፡፡ ጥላሁን በማኅበሩ ፕሬዝዳንትነቱ ቀዳሚው ሥራው የተማሪውን የመናገር፣ የመጻፍና የመደራጀት ነጻነት ይበልጥ ማጠናከርና የተለያዩ ሀሳቦች እንዲንሸራሸሩ መታገል ሆነ፡፡
ታህሳስ 19 ቀን 1962 ዓ.ም. ከታናሽ ወንድሙ መኮንን ሲሳይ ጋር በመሆን ከስድስት ኪሎ በስተጀርባ አፍንጮ በር በሚባለው አካባቢ ፍቅረኛውን ዮዲት ታዬን ለመሸኘት ወደ መኪና መንገድ ወጡ። ሰዓቱ በግምት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከሩብ ይሆናል። ታርጋ የሌላት አንድ መኪና ወደነጥላሁን ቀረብ በማለት የሞት ጥይቷን በጥላሁን ላይ አርከፈከፈችበት። ሕይወቱን ለማትረፍ የተደረገው ሙከራ ሳይሳካ ቀረና ጥላሁን ሞተ፡፡ ታኅሣስ 22 ቀን 1962 ዓ.ም የቀርብ ስርዓቱ በትውልድ አካባቢው ተፈፀመ፡፡
ጥላሁን ግዛው የቀዳማዊ አፄ ሃይለሥላሴ ልጅ፣ የልዑል መኮንን ባለቤት የሆኑት የልዕልት ሣራ ግዛው ወንድም ነው፡፡ ከባላባት ቤተሰብ ቢወለድም ዕድገቱ ግን ከአርሶ አደር ልጆች ጋር እንዲሁም በገጠር ኑሮው በአለባበሱም ሆነ በባህሪው ከአካባቢው ሕዝብ ጋር ለመመሳሰል ይጥር እንደነበር ይነገራል። በተማሪነት ዘመኑም ጊዜውን የሚያሳልፈው ከመሰል ተማሪ ጓደኞቹ ጋር እንጂ ከባለስልጣናትና ከከበርቴዎች ጋር አልነበረም። ልዩ የአንባቢነት ተሰጥኦም ነበረው፡፡
ታኅሳስ 20 ቀን 1900 ዓ.ም – በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያዋ መኪና አዲስ አበባ ከተማ ደረሰች፡፡ ዳግማዊ አፄ ምኒልክ ኢትዮጵያን ለማዘመን በነበራቸው ፍላጎት መኪና ወደ ኢትዮጵያ ለማስገባት ያላቸውን ጉጉት የሰማው እንግሊዛዊ ቤንትሌይ፣ ዌልስ ከተባለ ጓደኛው ጋር በመሆን የታርጋ ቁጥሯ ‹‹D3130›› የሆነች አውቶሞቢል ይዘው መኪናዋን በመርከብ ጭነው በባህር ላይ ጉዞ ጀመሩ፡፡
ጅቡቲን አልፈው ድሬዳዋ ሲደርሱ ደማቅ አቀባበልም ተደረገላቸው፡፡ ከዚያም በሐረር የሚገኙ መሳፍንትና መኳንንት መኪናዋን ማየት ስለፈለጉ መኪናዋን ይዘው ወደ ሐረር ሄዱ፡፡ በዚያ አካባቢም ጥቂት ሰንብተው ወደ አዲስ አበባ ጉዞ ጀመሩ፡፡
ታኅሣሥ 20 ቀን 1900 ዓ.ም አዲስ አበባ ሲደርሱ 2000 ባለፈረሰኛ ሰራዊት የክብር አቀባበል አደረገላቸው፤ መድፍ ተተኮሰ፡፡ እንግሊዛውያኑ የመኪናዋ አሽከርካሪዎችም የመኪናዋን ጥሩምባ እየነፉ አቀባበሉን አደመቁት፤ ፈረሶቹ ግን እየደነበሩ አስቸገሩ፡፡
ታኅሣሥ 21 ቀን 1900 ዓ.ም እንግዶቹ እቴጌ ጣይቱ ሆቴል ገብተው ግብዣ ተደረገላቸው፡፡ በማግሥቱ ታኅሣሥ 22 ቀን 1900 ዓ.ም ከረፋዱ አምስት ሰዓት ሲሆን ንጉሰ ነገሥት ዳግማዊ አጤ ምኒልክ መኪናዋን ተመለከቷት፡፡
ታኅሣሥ 21 ቀን 1938 ዓ.ም – የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተቋቋመ፡፡ አየር መንገዱ ከቀድሞው ትራንስ ወርልድ ኤይርዌይስ (Transworld Airways – TWA) ጋር በጋራ የተመሠረተ ሲሆን በወቅቱ አስተዳደሩ በአሜሪካውያን ቁጥጥር ስር ነበር፡፡ አየር መንገዱ የመጀመሪያውን ዓለም አቀፍ በረራ ያደረገው መጋቢት 30 ቀን 1938 ዓ.ም ሲሆን የበረራ መስመሩ ከአዲስ አበባ ወደ ካይሮ፣ ግብጽ ነበር፡፡
አየር መንገዱ በአሁኑ ወቅት በርካታ የመንገደኞችና የጭነት ማጓጓዣ አውሮፕላኖች፣ የራሱ የበረራና የጥገና ባለሙያዎች ማሰልጠኛ ማዕከልና ሌሎች ሀብቶች ያሉት የአፍሪካ ትልቁ አየር መንገድ ነው፡፡ ከታላላቅ ዓለም አቀፍ አየር መንገዶችም አንዱ መሆን የቻለ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምልክትና ኩራት ነው፡፡
ታኅሳሥ 23 ቀን 1917 ዓ.ም – በኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኃንና የጋዜጠኝነት ታሪክ ውስጥ ጉልህ ስፍራ የነበረው ‹‹ብርሃንና ሰላም›› ጋዜጣ ተመሰረተ (መታተም ጀመረ)፡፡ ‹‹ተፈሪ መኮንን ማተሚያ ቤት›› መስከረም 3 ቀን 1914 ዓ.ም በንጉሥ ተፈሪ መኮንን (የኋላው አፄ ኃይለሥላሴ) መኖሪያ ግቢ ውስጥ ጨው ቤት በሚባለው ባለ ሁለት ክፍል ቤት ውስጥ ስራውን ከሦስት ዓመታት ጀመረ በኋላ ‹‹ብርሃንና ሰላም›› የተባለውን ጋዜጣ ማተም ሲጀምር ስሙንም ከዚሁ ጋዜጣ ወረሰና ‹‹ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት›› ተባለ፡፡ ጊዜው ለኢትዮጵያ የብርሃንና የደስታ እንዲሆን በመመኘት ንጉሥ ተፈሪ መኮንን የጋዜጣውን ስያሜ ‹‹ብርሃንና ሰላም›› ብለው እንደሰየሙት ይነገራል፡፡
ታህሳሥ 23 ቀን 2010 ዓ.ም – በዘመናዊ የኢትዮጵያ የሕክምና ታሪክ ጉልህ ስፍራ ያላቸው፤በነበራቸው የማከም ጸጋና የማስተማር ክህሎት ለብዙዎች ምሳሌ መሆን የቻሉት አንጋፋው የሕክምና ጠቢብ ፕሮፌሰር ዕደማርያም ፀጋ አረፉ፡፡
ፕሮፌሰር ዕደማርያም በተለያዩ ሆስፒታሎች በሐኪምነትና በኃላፊነት ከማገልገላቸው በተጨማሪ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የመጀመሪያውን የኢንዶስኮፒ ማዕከል እንዲሁም በዘርፉ ስልጠና የሚሰጥበት የድህረ ምረቃ የትምህርት ክፍል እንዲቋቋም አድርገዋል፡፡
ኢትዮጵያውያን የሕክምና ትምህርት ተማሪዎች የሕመምተኛ የጤና ገጽታ አመዘጋገብ/የሕሙማን የምርመራ ሪፖርት አያያዝ መመሪያ (Medical Case Report) ትምህርትን የቀሰሙት የፕሮፌሰር ዕደማርያም ስራ ከሆነውና ‹‹A GUIDE TO WRITING MEDICAL CASE REPORTS›› ከተሰኘው አረንጓዴው መጽሐፍ ነው፡፡ በርካታ የምርምር ጽሑፎችን በአገርና ዓለም አቀፍ የምርምር መጽሔቶች ላይ አሳትመዋል፡፡
ታኅሣስ 24 ቀን 1895 ዓ.ም – የፊደል ገበታ አባትና አርበኛው ቀኛዝማች ተስፋ ገብረሥላሴ ተወለዱ፡፡ ቀኛዝማች ተስፋ ከ1921 ዓ.ም. ጀምሮ ማተሚያ ቤት በማቋቋም ‹‹እውቀት ይስፋ፤ድንቁርና ይጥፋ፤ይህ ነው የኢትዮጵያ ተስፋ›› የሚለውን ኃይለ ቃል አርዕስት በመስጠት ፊደልን፣ ፊደለ ሐዋርያንና አቡጊዳን በሦስት ረድፎች እያዘጋጁ በማሳተም በመላ ኢትዮጵያእንዲሰራጭ በማድረጋቸው በርካታ ኢትዮጵያውያን በተለይም በገጠራማ አካባቢዎች የሚኖሩ ሰዎች ከፊደላት ጋር ተዋወቁ፡፡ሪቻርድ ኒክሰን 37ኛው የአሜሪካ ፕሬዝደንት ስለመሆናቸው ኢንተርኔት ላይ check አድርጊ እስኪ፡፡ 37ኛው ካልሆኑ የመጨረሻው የታሪክ ክስተት (ማስታወሻ) ላይ አስተካክይው
በዚህ ሳምንት (ከታኅሳስ 26 እስከ ጥር 2) ከተከናወኑ አገራዊና ዓለም አቀፋዊ ታሪካዊ ክስተቶች መካከል:-
ታኅሳስ 26 ቀን 2010 ዓ.ም – የመጀመሪያው አፍሪካዊ የንግድ ጄት አብራሪ (The First Black African Commercial Jet Pilot) የሆኑት ኢትዮጵያዊው ካፒቴን ዓለማየሁ አበበ አረፉ፡፡
ካፒቴን ዓለማየሁ ገና ከአስር ዓመታቸው ጀምሮ አውሮፕላን በሰማይ ላይ ሲበር ሲያዩ አውሮፕላን አብራሪ የመሆን ሕልም ነበራቸው፡፡
ካፒቴን ዓለማየሁ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ለመቀላቀል የቻሉት በኢትዮጵያ አየር ኃይል በኩል በማለፍ ነው፡፡ በወቅቱ የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በከፍተኛ ውጤት ያጠናቀቁ ተማሪዎች ወደ አቪዬሽን ትምህርት እንዲገቡ ሲደረግ ከዕድሉ ተጠቃሚዎች መካከል አንዱ ካፒቴን ዓለማየሁ ነበሩ፡፡ ታሪካቸው እንደሚያመለክተው በአየር በነበራቸው የሥልጠና ጊዜ ከስዊድን የበረራ አሠልጣኞች የቀሰሙትን ሙያ በመጠቀም የመጀመርያውን የብቻ በረራ በ1938 ዓ.ም. ማድረግ ችለዋል፡፡ በዚያው ዓመት ለተጨማሪ የበረራ ትምህርት ወደ ስዊድን በመሄድ ትምህርታቸውን አጠናቀው ተመልሰዋል፡፡ ከስዊድን መልስም በደብረ ዘይት (ቢሾፍቱ) ከተማ በሚገኘው የአየር ኃይል መስሪያ ቤት ውስጥ በምክትል መቶ አለቃነት ማዕረግ የበረራ ክንፍ (ዊንግ) አግኝተዋል፡፡
በ1943 ዓ.ም. ምርጥ የሆኑ አብራሪዎች ከአየር ኃይል ወደ ኢትዮጵያ አየር መንገድ እንዲዛወሩ በተወሰነው መሠረት፣ ካፒቴን ዓለማየሁ ከተመራጮቹ አንዱ መሆን ችለው የኢትዮጵያ አየር መንገድን ተቀላቀሉ፡፡ ካፒቴን ዓለማየሁ ዓቢይ ተግባራቸውን ማከናወን የጀመሩት በ1950 ዓ.ም. የመጀመርያው የንግድ አውሮፕላን አዛዥ ሆነው ዲሲ-3/ሲ47 አውሮፕላንን ብቻቸውን በማብረር ነበር፡፡
በሦስት አስርታት ዓመታት የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአገልግሎት ዘመናቸውም ከመጀመርያ የበረራ መኰንንነት እስከ ካፒቴንነት (የመጀመርያው የቦይንግ 720B ጄት ካፒቴን) እስከ አየር መንገዱ የበረራ ዘርፍ ምክትልና ዋና ኃላፊነት (ከ1948 እስከ 1960 ዓ.ም.) ድረስ ሠርተዋል፡፡ ከ1961 እስከ 1972 ዓ.ም. ደግሞ የዓለም አቀፍ በረራዎች ዳይሬክተር፣ የበረራ ኦፕሬሽን ረዳት ጄኔራል ማኔጀር ሆነው አገልግለዋል፡፡ በ1968 ዓ.ም. የመጀመርያው አፍሪካዊ የቦይንግ 707 ጄት ካፒቴን ሆነው ሲሾሙ፣ በ1972 ዓ.ም የጄት ካፒቴኖች ፈታኝ በመሆን አገልግለዋል፡፡
ከኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ አገልግሎታቸውን በ1974 ዓ.ም. ፈጽመው ከተሰናበቱ በኋላ፣ በኡጋንዳና በየመን አየር መንገዶች ውስጥ በአሠልጣኝነትና በአማካሪነት ለአምስት ዓመታት ያህል ሰርተው የበረራ ምዕራፋቸውን ቋጭተዋል፡፡
ካፒቴን ዓለማየሁ አበበ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ስራ አስፈፃሚ የነበሩትን ኮሎኔል ስምረት መድኃኔን እንዳስተማሯቸው ታሪካቸው ያስረዳል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሚያሳትመው ‹‹ሰላምታ›› መጽሔት በአንድ ወቅት ባሳተመው ዕትሙ ላይ ‹‹የኢትዮጵያ አየር መንገድ ‹የአፍሪካ ስኬታማው አየር መንገድ› እንዲሆን ካስቻሉት ግንባር ቀደም ግለሰቦች መካከል ካፒቴን ዓለማሁ አበበ አንዱ ናቸው›› ብሎ ጠቅሷቸዋል፡፡
በሦስቱ የኢትዮጵያ መንግሥታት ዘመን በከፍተኛ የአገርና የሙያ ፍቅር አገራቸውን ያገለገሉት ካፒቴን ዓለማየሁ፣ ባለትዳርና የአራት ሴቶችና የአራት ወንዶች ልጆች አባት፣ እንዲሁም የአራት የልጅ ልጆች አያት ነበሩ፡፡ ዕውቅታቸውንና ልምዳቸውን ለተተኪው ትውልድ ለማስተላለፍ በማሰብም በ1997 ዓ.ም. ‹‹ሕይወቴ በምድርና በአየር›› የሚል መጽሐፍም አሳትመዋል፡፡
ካፒቴን ዓለማየሁ በተወለዱ በ93 ዓመታቸው፣ ታህሣሥ 26 ቀን 2010 ዓ.ም አርፈው ስርዓተ ቀብራቸው ታህሣሥ 28 ቀን 2010 ዓ.ም በጴጥሮስ ወጳውሎስ የካቶሊክ መካነ መቃብር ተፈጽሟል፡፡
ታኅሳስ 28 ቀን 1928 ዓ.ም – አንጋፋው የቅዱስ ጊዮርጊሥ እግር ኳስ ክብ ተመሰረተ፡፡ የክለቡ መስራቾችም አየለ አትናሽ እና ጆርጅ ዱካስ የተባሉ ጓደኛሞች እንደሆኑ የክለቡ ታሪክ ያስረዳል፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ ለ13 ጊዜያት ያህል የኢትዮጵያ ሻምፒዮን (የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ አሸናፊ) በመሆን ተወዳዳሪ አልተገኘለትም፡፡ የቡድኑ ቅፅል ስም ‹‹ፈረሰኞቹ›› ይሰኛል፡፡ ‹‹ፈረሰኞቹ›› ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ በተጨማሪ ሌሎች በርካታ ድሎችንም ተጎናጽፈዋል፡፡
ለቅዱስ ጊዮርጊስ ለረዥም ጊዜያት በመሰለፍ ቀዳሚዎቹ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ላይ ታላቅ ስም ያላቸው ይድነቃቸው ተሰማ (ለ23 ዓመታት) እና መንግሥቱ ወርቁ (ለ16 ዓመታት) ናቸው፡፡
ጥር 1 ቀን 1905 ዓ.ም – ‹‹የወተርጌት ቅሌት (The Watergate Scandal)›› በተባለው ክስተት ስልጣናቸውን የለቀቁት 37ኛው የአሜሪካ ፕሬዝደንት ሪቻርድ ኒክሰን በካሊፎርኒያ ግዛት ተወለዱ፡፡ ሪቻርድ ሚልሀውስ ኒክሰን የአሜሪካ ፕሬዝደንት ከመሆናቸው አስቀድሞ የፕሬዝደንት ዲዋይት ደቪድ አይዘንሐወር ምክትል ሆነው አገልግለዋል፡፡ ምክትል ፕሬዝደንት በነበሩበት ወቅት ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ነበር፡፡በዚህ ሳምንት (ከታኅሳስ 26 እስከ ጥር 2) ከተከናወኑ አገራዊና ዓለም አቀፋዊ ታሪካዊ ክስተቶች መካከል:-
ታኅሳስ 26 ቀን 2010 ዓ.ም – የመጀመሪያው አፍሪካዊ የንግድ ጄት አብራሪ (The First Black African Commercial Jet Pilot) የሆኑት ኢትዮጵያዊው ካፒቴን ዓለማየሁ አበበ አረፉ፡፡
ካፒቴን ዓለማየሁ ገና ከአስር ዓመታቸው ጀምሮ አውሮፕላን በሰማይ ላይ ሲበር ሲያዩ አውሮፕላን አብራሪ የመሆን ሕልም ነበራቸው፡፡
ካፒቴን ዓለማየሁ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ለመቀላቀል የቻሉት በኢትዮጵያ አየር ኃይል በኩል በማለፍ ነው፡፡ በወቅቱ የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በከፍተኛ ውጤት ያጠናቀቁ ተማሪዎች ወደ አቪዬሽን ትምህርት እንዲገቡ ሲደረግ ከዕድሉ ተጠቃሚዎች መካከል አንዱ ካፒቴን ዓለማየሁ ነበሩ፡፡ ታሪካቸው እንደሚያመለክተው በአየር በነበራቸው የሥልጠና ጊዜ ከስዊድን የበረራ አሠልጣኞች የቀሰሙትን ሙያ በመጠቀም የመጀመርያውን የብቻ በረራ በ1938 ዓ.ም. ማድረግ ችለዋል፡፡ በዚያው ዓመት ለተጨማሪ የበረራ ትምህርት ወደ ስዊድን በመሄድ ትምህርታቸውን አጠናቀው ተመልሰዋል፡፡ ከስዊድን መልስም በደብረ ዘይት (ቢሾፍቱ) ከተማ በሚገኘው የአየር ኃይል መስሪያ ቤት ውስጥ በምክትል መቶ አለቃነት ማዕረግ የበረራ ክንፍ (ዊንግ) አግኝተዋል፡፡
በ1943 ዓ.ም. ምርጥ የሆኑ አብራሪዎች ከአየር ኃይል ወደ ኢትዮጵያ አየር መንገድ እንዲዛወሩ በተወሰነው መሠረት፣ ካፒቴን ዓለማየሁ ከተመራጮቹ አንዱ መሆን ችለው የኢትዮጵያ አየር መንገድን ተቀላቀሉ፡፡ ካፒቴን ዓለማየሁ ዓቢይ ተግባራቸውን ማከናወን የጀመሩት በ1950 ዓ.ም. የመጀመርያው የንግድ አውሮፕላን አዛዥ ሆነው ዲሲ-3/ሲ47 አውሮፕላንን ብቻቸውን በማብረር ነበር፡፡
በሦስት አስርታት ዓመታት የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአገልግሎት ዘመናቸውም ከመጀመርያ የበረራ መኰንንነት እስከ ካፒቴንነት (የመጀመርያው የቦይንግ 720B ጄት ካፒቴን) እስከ አየር መንገዱ የበረራ ዘርፍ ምክትልና ዋና ኃላፊነት (ከ1948 እስከ 1960 ዓ.ም.) ድረስ ሠርተዋል፡፡ ከ1961 እስከ 1972 ዓ.ም. ደግሞ የዓለም አቀፍ በረራዎች ዳይሬክተር፣ የበረራ ኦፕሬሽን ረዳት ጄኔራል ማኔጀር ሆነው አገልግለዋል፡፡ በ1968 ዓ.ም. የመጀመርያው አፍሪካዊ የቦይንግ 707 ጄት ካፒቴን ሆነው ሲሾሙ፣ በ1972 ዓ.ም የጄት ካፒቴኖች ፈታኝ በመሆን አገልግለዋል፡፡
ከኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ አገልግሎታቸውን በ1974 ዓ.ም. ፈጽመው ከተሰናበቱ በኋላ፣ በኡጋንዳና በየመን አየር መንገዶች ውስጥ በአሠልጣኝነትና በአማካሪነት ለአምስት ዓመታት ያህል ሰርተው የበረራ ምዕራፋቸውን ቋጭተዋል፡፡
ካፒቴን ዓለማየሁ አበበ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ስራ አስፈፃሚ የነበሩትን ኮሎኔል ስምረት መድኃኔን እንዳስተማሯቸው ታሪካቸው ያስረዳል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሚያሳትመው ‹‹ሰላምታ›› መጽሔት በአንድ ወቅት ባሳተመው ዕትሙ ላይ ‹‹የኢትዮጵያ አየር መንገድ ‹የአፍሪካ ስኬታማው አየር መንገድ› እንዲሆን ካስቻሉት ግንባር ቀደም ግለሰቦች መካከል ካፒቴን ዓለማሁ አበበ አንዱ ናቸው›› ብሎ ጠቅሷቸዋል፡፡
በሦስቱ የኢትዮጵያ መንግሥታት ዘመን በከፍተኛ የአገርና የሙያ ፍቅር አገራቸውን ያገለገሉት ካፒቴን ዓለማየሁ፣ ባለትዳርና የአራት ሴቶችና የአራት ወንዶች ልጆች አባት፣ እንዲሁም የአራት የልጅ ልጆች አያት ነበሩ፡፡ ዕውቅታቸውንና ልምዳቸውን ለተተኪው ትውልድ ለማስተላለፍ በማሰብም በ1997 ዓ.ም. ‹‹ሕይወቴ በምድርና በአየር›› የሚል መጽሐፍም አሳትመዋል፡፡
ካፒቴን ዓለማየሁ በተወለዱ በ93 ዓመታቸው፣ ታህሣሥ 26 ቀን 2010 ዓ.ም አርፈው ስርዓተ ቀብራቸው ታህሣሥ 28 ቀን 2010 ዓ.ም በጴጥሮስ ወጳውሎስ የካቶሊክ መካነ መቃብር ተፈጽሟል፡፡
ታኅሳስ 28 ቀን 1928 ዓ.ም – አንጋፋው የቅዱስ ጊዮርጊሥ እግር ኳስ ክብ ተመሰረተ፡፡ የክለቡ መስራቾችም አየለ አትናሽ እና ጆርጅ ዱካስ የተባሉ ጓደኛሞች እንደሆኑ የክለቡ ታሪክ ያስረዳል፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ ለ13 ጊዜያት ያህል የኢትዮጵያ ሻምፒዮን (የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ አሸናፊ) በመሆን ተወዳዳሪ አልተገኘለትም፡፡ የቡድኑ ቅፅል ስም ‹‹ፈረሰኞቹ›› ይሰኛል፡፡ ‹‹ፈረሰኞቹ›› ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ በተጨማሪ ሌሎች በርካታ ድሎችንም ተጎናጽፈዋል፡፡
ለቅዱስ ጊዮርጊስ ለረዥም ጊዜያት በመሰለፍ ቀዳሚዎቹ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ላይ ታላቅ ስም ያላቸው ይድነቃቸው ተሰማ (ለ23 ዓመታት) እና መንግሥቱ ወርቁ (ለ16 ዓመታት) ናቸው፡፡
ጥር 1 ቀን 1905 ዓ.ም – ‹‹የወተርጌት ቅሌት (The Watergate Scandal)›› በተባለው ክስተት ስልጣናቸውን የለቀቁት 37ኛው የአሜሪካ ፕሬዝደንት ሪቻርድ ኒክሰን በካሊፎርኒያ ግዛት ተወለዱ፡፡ ሪቻርድ ሚልሀውስ ኒክሰን የአሜሪካ ፕሬዝደንት ከመሆናቸው አስቀድሞ የፕሬዝደንት ዲዋይት ደቪድ አይዘንሐወር ምክትል ሆነው አገልግለዋል፡፡ ምክትል ፕሬዝደንት በነበሩበት ወቅት ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ነበር፡፡
በዚህ ሳምንት (ከጥር 3 እስከ ጥር 9) ከተከናወኑ አገራዊ ታሪካዊ ክስተቶች መካከል:-
ጥር 3 ቀን 1893 ዓ.ም – የጎጃም ንጉስ የነበሩት፣ ንጉሥ ተክለሃይማኖት ተሰማ አረፉ፡፡ ንጉሥ ተክለሃይማኖት የልጅነት ስማቸው ‹‹አዳል›› ነበር፡፡ በእርሳቸው የልጅነት ዘመን የጎጃም መስፍን የነበሩት ደጃዝማች ተድላ ጓሉ ነበሩ፡፡ ደጃዝማች ተድላ ጓሉ እና ልጅ አዳል ተሰማ (ንጉሥ ተክለሃይማኖት) የቅርብ ዘመዶች ናቸው፡፡
ደጃዝማች ተድላ ጓሉ ሕዳር 6 ቀን 1860 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ሲለዩ ልጅ አዳል ተሰማ ተቀናቃኞቻቸውን አሸንፈው ‹‹ራስ›› በሚል ማዕረግ፣ ተከፋፍሎ የነበረውን የጎጃምን ግዛት አንድ አድርገው ማስተዳደር ጀመሩ፡፡ በወቅቱ የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገሥት የነበሩት አፄ ዮሐንስ ፬ኛ ራስ አዳል ተሰማን ጥር 11 ቀን 1873 ዓ.ም ‹‹ንጉስ ተክለሃይማኖት›› ብለው አነገሷቸው፡፡
ንጉሥ ተክለሃይማኖትም መናገሻቸውን ደብረ ማርቆስ አድርገው እስከ ዕለተ ሞታቸው ድረስ አብያተ-ክርስቲያናትን በማሳነፅና አገር በማቅናት ቆይተዋል፡፡ በዓድዋ ጦርነት ጊዜም ጦራቸውን ይዘው ወደ ዓድዋ በመዝመት ታላቅ ጀብድ ፈፅመዋል፡፡
ጥር 5 ቀን 1937 ዓ.ም – ጀግናው አርበኛ ደጃዝማች በላይ ዘለቀ (አባ ኮስትር) እና ወንድማቸው እጅጉ ዘለቀ ተገደሉ (በስቅላት ተቀጡ)፡፡
በላይ ዘለቀ ከአባታቸው ባሻ ዘለቀ ላቀው እና ከእናታቸው ወይዘሮ ጣይቱ አስኔ በ1904 ዓ.ም ተወለዱ። አባታቸው ባሻ ዘለቀ ላቀው የልጅ ኢያሱ ሚካኤል አንጋች (ባለሟል) ነበሩ፡፡ በላይ ገና ልጅ ሳሉ አባታቸው በሰው እጅ በመገደላቸው ምክንያት በእናታቸው እንክብካቤ ያለአባት አደጉ። እድሜያቸው እየጨመረ ሲመጣም የአባታቸው ገዳይ ማን እንደሆነ በማወቅ ለመበቀል ገዳዩን ማፈላለግ ጀመሩ።
ፋሺስት ኢጣሊያ ኢትዮጵያን በወረረች ጊዜ በላይም ዘለቀ ሀገርን የወረረውን የኢጣሊያን ጦር ለመውጋት ቆርጠው ተነሱ። ብዙ ተከታዮችን በማፍራትም ወደ አርበኝነት ገቡ፡፡ ጀግናው አርበኛ ከፋሺሽት ኢጣሊያ ጋር ባደሩጓቸው ተደጋጋሚ ውጊያዎች ታላላቅ ድሎችን አስመዘግበው በርካታ የኢጣሊያና የባንዳ ወታደሮችን በመማረክና በመግደል እንዲሁም የጠላት ጦር ካምፖችን በማቃጠል ታላላቅ ጀብዶችን ፈፀሙ፡፡